ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ቲፒ ማዜምቤ
Entrance : በትኬት
 • General

  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ቲፒ ማዜምቤ የሚያደርገው ጨዋታ መጋቢት 4 ቀን በባህርዳር ከተማ ያደርጋል

  ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሲሸልሱ ቅዱስ ሚካኤል ቡድን በድምሩ አራት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፎ ካለፈ በኋላ በሁለተኛው ዙር ጨዋታ መጋቢት አራት ቀን 2008 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በሚገኘው ዘመናዊ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተረጋግጧል፡፡

  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቲፒ ማዜምቤ ታሪካዊ ዳራ

  የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ክለባች ሻምፒዮናን ማዘጋጀት የጀመረው እ.ኤ.አ በ1964 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ በ1956 ዓ.ም ነበር፡፡ በወቅቱ ይህ ውድድር ሲዘጋጅ በተሳታፊነት የቀረቡት ክለቦች አራት ብቻ ሲሆኑ የዙር ውድድራቸውን ያደረጉትም በጋና አክራና ኩምሊ በተባሉት ከተሞች ላይ ነበር፡፡

  በአራት ክለቦች እና በሁለት ከተሞች ላይ ብቻ ውድር በማድረግ የጀመረው የአፍሪካ ክለባች ሻምፒዮና አሁን እያደገ ሄዶ ከፊፊ ፊዴሬሽኖች የተወጣጡ 52 ቡድኖች ተካፋይ ሆነውበታል፡፡

  በዚህ ውድድር ስምንት ውስጥ ለመግባት ሦስት የማጣሪያ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ እንደሚታውቀው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ባሳለፍነው ሳምንት የሲሸየልሱን ቅዱስ ሚካኤልን ቡድንን አራት ለአንድ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ማጣሪያ ማለፉ ይታወሳል፡፡

  በሁለተኛው ማጣሪያም የኮንጐውን ወካይ ክለብ ቲፒ ማዜምቤ ክለብን ማግኘቱ ይታወቃል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ለዚህ ውድድር ሲገናኙ ለሁለተኛ ግዘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ1958 ዓ.ም ነበር፡፡

  ሁለቱ ቡድኖች የተገናኙት በ1958 ዓ.ም በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ሀገራችንን በመወከል የተካፈለው ቅዱስ ጊዮርጊስ በወጣው የጨዋታ ድልድል መሰረት ከኡጋንዳው ክለብ ፎርፌ በማግኘት ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ በቅቷል፡፡

  በሁለተኛው የማጣሪያ ውድድር የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ ሆኖ የቀረበው የግብጹ አሌክሳንድርያ ክለብ ነበር፡፡

  When
  መጋቢት 4 ቀን 2008
  Where
  በባህርዳር ከተማ እስታድየም
  Interest
 • Organizer

  The Ethiopian Football Federation (EFF) is the governing body of football in Ethiopia. It was founded in 1943 and became affiliated with FIFA in 1952 and with CAF in 1957. It organizes the national football league and the national team.